መዝሙር 71:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝብህን በጽድቅ፥ ድሆችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽድቅህም ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጽድቅህ ከችግር እንዳመልጥ አድርገህ አውጣኝ አድምጠህም አድነኝ። |
እግዚአብሔር ኀይሌ፥ አምባዬ፥ መድኀኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬም ነው።
በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ በቤተ መቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
በሰው ላይ እንደሚደርሰው ያለ ፈተና ነው እንጂ ሌላ ፈተና አያገኛችሁም። በምትችሉት መከራ ነው እንጂ በማትችሉት መከራ ትፈተኑ ዘንድ ያልተዋችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፤ እርሱም ከፈተና ትድኑ ዘንድ በመከራ ጊዜ ይረዳችኋል።