እሰይ! እሰይ! የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
በጩኸት ደከምሁ፤ ጕረሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ፣ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።
ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
የኃጥኣን መድኀኒታቸው ታልቃለች። ተስፋቸውንም ያጣሉ፥ የዝንጉዎች ዐይኖችም ይጠፋሉ።”
በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከራዬ በመሬት ላይ በዛች።
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ።
በዚያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።
በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
እግዚአብሔር በቅዱሳን ምክር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።
እንደ ሸመላ እንዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ባየ ጊዜ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ራሳቸውንም ሲመቱአቸው በዐይኖችህ ታያለህ፤ ልታደርገውም የምትችለው የለም።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።