መዝሙር 68:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ፥ የሚሹህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይነወሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በቅዱስ መኖሪያው ወላጅ ለሞቱባቸው አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበትን ቤት ይሰጣቸዋል፤ እስረኞች ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ። |
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ዕራቁትዋንም እንድትቆም አደርጋታለሁ፤ እንደ ሕፃንነትዋ ወራት፥ እንደ ተወለደችባት እንደ መጀመሪያዪቱም ቀን አደርጋታለሁ። እንደ ምድረ በዳም አደርጋታለሁ፤ ውኃም እንደሌላት ምድር አደርጋታለሁ፤ በውኃም ጥም እገድላታለሁ።
ድንገትም ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ፤ የወህኒ ቤቱ መሠረትም ተናወጠ፤ በሮችም ሁሉ ያንጊዜ ተከፈቱ፤ የሁሉም እግር ብረቶቻቸው እየወለቁ ወደቁ።
“የማትወልድ መካን ደስ ይላታል፤ ምጥ የማታውቀውም ደስ ብሎአት እልል ትላለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈቲቱ ልጆች ብዙዎች ናቸውና” ተብሎ ተጽፎአል።
እንጀራ ጠግበው የነበሩ ተራቡ፤ ተርበውም የነበሩ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው መውለድ አልቻለችም።