Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 16:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ድን​ገ​ትም ታላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ሆነ፤ የወ​ህኒ ቤቱ መሠ​ረ​ትም ተና​ወጠ፤ በሮ​ችም ሁሉ ያን​ጊዜ ተከ​ፈቱ፤ የሁ​ሉም እግር ብረ​ቶ​ቻ​ቸው እየ​ወ​ለቁ ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በድንገት የወህኒ ቤቱ መሠረት እስኪናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ በሮቹም ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከፈቱ፤ የእያንዳንዱም እስረኛ ሰንሰለት ተፈታ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 16:26
15 Referencias Cruzadas  

ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ግን በሌ​ሊት የወ​ኅኒ ቤቱን ደጃፍ ከፍቶ አወ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው።


መጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንና ሁለ​ተ​ኛ​ውን ዘብ አል​ፈው ወደ ከተማ ወደ​ም​ት​ወ​ስ​ደው ወደ ብረቱ መዝ​ጊያ ደረሱ፤ ያን​ጊ​ዜም መዝ​ጊ​ያው ራሱ ተከ​ፈ​ተ​ላ​ቸው፤ ወጥ​ተ​ውም በአ​ንድ ስላች መን​ገድ ሄዱ፤ መል​አ​ኩም ጴጥ​ሮ​ስን ትቶት ሄደ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ስ​ጋና ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በመ​ሰ​ንቆ ዘምሩ፤


እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።


የዕ​ው​ራ​ን​ንም ዐይን ትከ​ፍት ዘንድ፥ የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም ከግ​ዞት ቤት፥ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከወ​ህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።


ቃሉን የም​ት​ፈ​ጽሙ፥ ብር​ቱ​ዎ​ችና ኀያ​ላን፥ የቃ​ሉ​ንም ድምፅ የም​ት​ሰሙ መላ​እ​ክቱ ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።


ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋ​ንም እስከ ባሕር፥ ቡቃ​ያ​ዋ​ንም እስከ ወንዙ ዘረ​ጋች።


ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤


አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።


ሄዶም፥ ሬሳው በመ​ን​ገድ ወድቆ፥ በሬ​ሳ​ውም አጠ​ገብ አህ​ያ​ውና አን​በ​ሳው ቆመው፥ አን​በ​ሳ​ውም ሬሳ​ውን ሳይ​በ​ላው፥ አህ​ያ​ው​ንም ሳይ​ሰ​ብ​ረው አገኘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios