Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እግዚአብሔር በቅዱስ መኖሪያው ወላጅ ለሞቱባቸው አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበትን ቤት ይሰጣቸዋል፤ እስረኞች ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:6
18 Referencias Cruzadas  

መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ።


እግዚአብሔር ድኾችን ይሰማልና፤ በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።


ከጨለማና ከጥልማሞት አወጣቸው፤ እስራታቸውንም በጠሰላቸው።


አንዳንዶቹ በብረት ሰንሰለት ታስረው የተጨነቁ፣ በጨለማ፣ በጥልማሞት ውስጥ የተቀመጡ ነበሩ፤


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤


እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ በእልልታ ጩኺ፤ ባል ካላት ይልቅ፣ የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።”


ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።


ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።


ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።


ዔሳውን ግን ጠላሁ፤ ተራሮቹን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁበት።”


አለዚያ ገፍፌ ዕርቃኗን አስቀራታለሁ፤ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፤ እንደ ምድረ በዳ፣ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።


እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል።


አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።


ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤ እርሱ ይፋረድላቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios