ትልምዋን አርካው፥ መከሯንም አብጀው፤ በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች
ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይበለው፤ እርሱንም መጠጊያ ያድርገው፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ደስ ይበላቸው።
ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።
ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤ ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።
ጻድቃንም አይተው ሳቁ፤ ንጹሓንም በንቀት ይዘባበቱባቸዋል።
አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን።
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።
የአምላኬ ይቅርታው ይድረሰኝ አምላኬ በጠላቶቼ ላይ አሳየኝ።
እኔ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓለሙ ዘንድ የሞትሁ ነኝ።
ዘወትር በጌታችን ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላችኋለሁ፦ ደስ ይበላችሁ።