መዝሙር 62:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጡ፥ የቀበሮዎችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፥ በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በብዝበዛ አትመኩ፤ በቀማችሁትም ነገር ለመክበር ተስፋ አታድርጉ፤ ሀብታችሁ ቢበዛ እንኳ በእርሱ አትተማመኑ። |
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፥ “ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በሐሰትና በጠማማነት ተስፋ አድርጋችኋልና፥ አጕረምርማችኋልምና፥ በዚህም ቃል ታምናችኋልና፤
በክፋትሽ ታምነሻል፤ አንቺ ግን፥ “እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብለሻል፤ በዝሙትሽ ኀፍረት ያሰብሽውንም ዕወቂ፤ በልብሽ፥ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻልና።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን የምወድድ፥ ስርቆትንና ቅሚያን የምጠላ ነኝ፤ እንደ ሥራቸውም ለጻድቃን እከፍላቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።