መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
መዝሙር 60:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፤ ይቅርታውንና ጽድቁን ማን ይፈልጋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴ የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤ ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን፥ “በራሳችን ላይ ጉዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እርሱ አልረዳቸውም።
በዮርዳኖስም ማዶ ካሉ ከሮቤልና ከጋድ ሰዎች ከምናሴም ነገድ እኩሌታ የጦር መሣሪያንም ሁሉ ይዘው የመጡ መቶ ሃያ ሺህ ነበሩ።
ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስጣሮትና ኤድራይን ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች እኩሌታም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
የምናሴ ልጆች ነገድ ድንበር ይህ ነው፤ የዮሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የምናሴም በኵር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።
ዳዊትም አንኩስን፥ “አሁን አገልጋይህ የሚያደርገውን ንገረው” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ” አለው።