አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤ ገረፍኸን፥ ይቅርም አልኸን።
አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
አምላክ ሆይ! ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ።
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
አቤቱ፥ በአዲስ ምስጋና አመሰግንሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ።
አቤቱ፥ በኀይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህም እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
በእውነት ጽድቅን ብትናገሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁ፤
አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶች አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
ለድሆች ሕዝብህ በጽድቅ ፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች አድናቸው። ትዕቢተኛውንም አዋርደው።
ያንጊዜ በመልካም ሽምግልና ይበዛሉ፤ ዕረፍት ያላቸውም ሆነው ይኖራሉ።
እርሱ ከፍ ባለ በጽኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖራል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፤ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።