መዝሙር 55:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቃሌን አከብራለሁ፤ የተናገርሁትም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንና ሌሊት ቅጥሯ ላይ ወጥተው ይዞሯታል፤ ተንኰልና መከራ በውስጧ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቼአለሁና አስጥማቸው አንደበታቸውንም ቁረጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግርና ጥፋት የሞላባት ነች። ክፉዎችም ቀንና ሌሊት በቅጽሮችዋ ይዞራሉ። |
እግዚአብሔርም፥ “በከተማዪቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ኀጢአት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ ጋጋሪያቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል።
ጌታችን ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት፤ አይሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋሲካውን በግ ሳይበሉ እንዳይረክሱ ወደ ፍርድ አደባባይ አልገቡም።
ይሁዳም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ወታደሮችን ተቀበለ፤ ሎሌዎቻቸውንም በረዳትነት ወሰደ፤ ፋኖስና የችቦ መብራት፥ የጦር መሣሪያም ይዞ ወደዚያ ሄደ።
ሳውል ግን በእርሱ ላይ ሊያደርጉት የሚሹትን ዐወቀባቸው፤ ሊገድሉትም በቀንና በሌሊት የከተማውን በር ይጠብቁ ነበር።
ሳኦልም ዳዊትን ጠበቀው፤ በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስቱም ሜልኮል፥ “በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ” ብላ ነገረችው።