እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፥ በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኀይልና ችሎታ በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።
መዝሙር 54:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጠኝ፥ ልመናዬንም ቸል አትበለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ። |
እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፥ በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኀይልና ችሎታ በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ ቍጣውም ከከንፈሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነድዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተመላ ነው፤ የቍጣውም መቅሠፍት እንደምትበላ እሳት ናት፤
የሚቤዢአቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያሳርፍ ዘንድ፥ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ጠላቶቹን ወቀሳ ይወቅሳቸዋል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ኮረብታው ወደ ሳኦል መጥተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸሽጎ አለ” አሉት።