በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥
ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤ እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።
አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አስተንትኖ ማስተዋልን።
ሐሳቤን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፤ የምሳሌዎችንም ትርጒም በገና በመደርደር እገልጣለሁ።
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፤
ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።
እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ አይሁን አልሁ፤ እነርሱ ግን፦ ይህ የነገረን ምሳሌ አይደለምን? ይሉኛል።”
እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፤ በስውርም አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ያያል፤ አገልጋዬ ሙሴን ማማትን ስለ ምን አልፈራችሁም?” አለ።
በምሳሌም ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ከሜስጴጦምያ ጠርቶ አመጣኝ፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ።
በጨለማ የምትናገሩት በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትንሾካሾኩት በሰገነት ይሰበካል።
እንግዲህ ይህን ያህል ተስፋ ካለን በግልጥ ፊት ለፊት ልንቀርብ እንችላለን።