በኀይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚኮሩ፤
ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው።
እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ሸሹም።
እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤ ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።
ስለዚህም ተነሥተው በጨለማ ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውንና ፈረሶቻቸውን፥ አህዮቻቸውንና ሰፈሩን እንዳለ ትተው ነፍሳቸውን ያድኑ ዘንድ ሸሹ።
ስለዚህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕማሜ የተነሣ አልሰማም፤ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።
ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይዘዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋቂም አይደለም፤ በልጆችም ተግሣጽ አይጸናም።