La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 48:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መቃ​ብ​ራ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ነው፥ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ስማ​ቸው ይጠ​ራል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለ ፍርድህ፣ የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤ የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።

Ver Capítulo



መዝሙር 48:11
17 Referencias Cruzadas  

የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።


ወን​ዞ​ችም በአ​ን​ድ​ነት በእጅ ያጨ​ብ​ጭቡ፥ ተራ​ሮች ደስ ይበ​ላ​ቸው፥


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ፥ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽናት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦ ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ቀላል አድ​ር​ጋ​ሃ​ለች፤ በን​ቀ​ትም ሥቃ​ብ​ሃ​ለች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ ራስ​ዋን ነቅ​ን​ቃ​ብ​ሃ​ለች።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጆች ሆይ፥ ለራ​ሳ​ች​ሁና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አል​ቅሱ እንጂ ለእ​ኔስ አታ​ል​ቅ​ሱ​ልኝ።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።