ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ። በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ ብሎአል።
መዝሙር 46:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለርስቱ እኛን መረጠን፥ የያዕቆብን ውበት የወደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ከተማ፣ የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ የወንዝ ፈሳሾች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆቻቸው እየገነፈሉ ጮኹ፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተንቀጠቀጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥ የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች። |
ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ። በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ ብሎአል።
በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥ ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለሃቸዋልና።
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።
በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤