መዝሙር 44:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ለዓለምና ለዘለዓለም። አሕዛብ ያመሰግኑሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን ሳንረሳ፣ ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣ ይህ ሁሉ ደረሰብን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሚሳደብና ከሚላገድ ቃል የተነሣ፥ ከጠላትና ከቂመኛ ፊት የተነሣ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ የደረሰብን አንተን ሳንረሳና ቃል ኪዳንህንም ሳናፈርስ ነው። |
አዳኝህ እግዚአብሔርን ትተኸዋልና፥ ረዳትህ እግዚአብሔርንም አላስብኸውም፤ ስለዚህ የሐሰትን ተክል ተክለሃል፤ የሐሣርንም ዘር ዘርተሃል።
ከግብፅ ሀገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
“ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳንን በማፍረስ መሐላን የናቅሽ ሆይ! አንቺ እንዳደረግሽ እኔ ደግሞ አደርግብሻለሁ።