ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ በወርቀ ዘቦ ልብስ የተጐናጸፈችና የተሸፋፈነች ናት።
ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
ሕዝብህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥ በመለወጣቸውም ትርፍ የለም።
በጐረቤቶቻችን የምንነቀፍ አደረግኸን፤ በዙሪያችን ላሉትም መዘባበቻና መሳለቂያ አደረግኸን።
የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ በባሪያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
ጀርባውን ከመስገጃቸው መለሰ፥ እጆቹም በቅርጫት ተገዙ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በከንቱ ተሸጣችሁ ነበር፤ ያለ ወርቅም እቤዣችኋለሁ።”
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
እግዚአብሔርም ወደ እነርሱ በሚወስድህ አሕዛብ መካከል ሁሉ የደነገጥህ፥ ለምሳሌና ለተረትም ትሆናለህ።