“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
መዝሙር 43:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅህ ጠላትን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ ለምን ተውኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤ ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ? ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ? |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲፈልጉ፤
እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።