ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ።
ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።
ምናልባት መከራዬን አይቶ ስለ ርግማኑ በዚህ ቀን መልካም ይመልስልኛል” አላቸው።
ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
እኔም ከራሴ ጀምሮ፥ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦ “አምላክሽ አያድንሽም።”
ከክፉዎች ሴራ ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።
ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።
አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይበላታል።
ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ። የማያውቀውን ቋንቋ ሰማ።
መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፤ ከቍጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።
የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት በወለሉና በምሥዋዑ መካከል እያለቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብም ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብም መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።
ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።
ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት መካከል ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወት የኖረ ማን ነው?