መዝሙር 39:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም፤ የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፤ በእርግጥ ሰው ከነፋስ ሽውታ የሚሻል አይደለም። |
ይልቁንም ከአንድ ዐይነት ጭቃ የተፈጠርን እኛ፥ በተፈጠርንበት የጭቃ ቤት የሚኖሩትን እንደ ብል ይጨፈልቃቸዋል።
ሥጋውን ጎድቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።
እግዚአብሔር የሚወደውን ይገሥጻልና፥ የሚወደደውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል” ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።