መዝሙር 38:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝም አልሁ ራሴንም አዋረድሁ፥ ለበጎ ነገርም ዝም አልሁ፥ ቍስሌም ታደሰብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤ እጅህም ተጭናኛለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍላጻዎችህ ወግተኸኛል፤ በብርቱ እጅህም መተኸኛል። |
እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፣ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ” አሉ።
የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ።
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”