መዝሙር 35:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ። አቤቱ፥ ምሕረትህን እንደ አበዛህ፥ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤ ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረውላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥ ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤ እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል። |
በጽድቅ ገሥጸኝ፥ በምሕረትም ዝለፈኝ፥ የኀጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
አቤቱ፥ የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፥ ደስም ይበላቸው፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ፥ “ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።