መዝሙር 33:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የጌታ ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በቸርነቱም ወደሚታመኑ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሚፈሩትንና ዘለዓለማዊ ፍቅሩ ተስፋቸው የሆነውን ይመለከታል። |
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ንጉሡንም፥ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኀይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና፤ በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና።
ዐይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፤ ለዘለዓለም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ በድል አድራጊነትም ያኖራቸዋል። እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።