መዝሙር 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህች ትውልድ እርሱን ትፈልገዋለች፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት ትፈልጋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በጎነትና ምሕረት በርግጥ ይከተሉኛል፤ እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣ ለዘላለም እኖራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸርነትና ምሕረት በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖራለሁ። |
አቤቱ፥ ከተግሣጽህ፥ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን።
በእነዚህ በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከክርስቶስም ዘንድ ልኖር እወዳለሁ፤ ይልቁንም ለእኔ ይህ ይሻለኛል፤ ይበልጥብኛልም።