“በእግዚአብሔር አመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ከወደደው ያድነው።”
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች።
ንጉሥ በጌታ ተማምኖአልና፥ በልዑልም ጽኑ ፍቅር አይናወጥም።
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ፥ ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ሁሉ ያገኛል።
እንዲህም ሆነ፤ ንጉሡ በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ እግዚአብሔርም በዙሪያው ያሉ ጠላቶቹን ሁሉ ባወረሰው ጊዜ፥
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ።”
አፋቸውንም በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ላይ ተመላለሰ።
ይሁዳንም እንዲሁ አደርጋታለሁ፤ በኢየሩሳሌምና በሰማርያ የሚያድን ጣዖት አለን?
የሀገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነግሥ አንሻም ብለው አከታትለው መልእክተኞችን ላኩ።
ነገር ግን እነዚያን ልነግሥባቸው ያልወደዱትን ጠላቶችን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ውጉአቸው።”
ጠላቶቹ ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪወድቁ ድረስ ይነግሥ ዘንድ አለውና።
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።
የሚያሳድድህና ነፍስህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሕይወት ማሰሪያ የታሰረች ትሆናለች፤ የጠላቶችህ ነፍስ ግን በወንጭፍ እንደሚወነጨፍ ትሁን።
ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፤ ቀስተኞችም አገኙት፤ ታፋውንም ወጉት።