ቃላቸው ያልተሰማበት ነገር የለም፥ መናገርም የለም፥
ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
ጌታ ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ዓለቴ፥ ጋሻዬ፥ የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።
ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ እርሱም ከጠላቶቼ ያድነኛል።
ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለም አመሰግናለሁ።
ማዳን በማይችሉ በአለቆችና በሰው ልጆች አትታመኑ።
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ።
በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ እሾህ በወጋኝ ጊዜ ወደ ጕስቍልና ተመለስሁ።
አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩም ሁላችሁ፥ አድምጡ፤
አቤቱ፥ ከንፈሮችን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።
ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና፥ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
ተራሮችና ኮረብቶች የሕዝብህን ሰላም ይቀበሉ።
ደነገጥሁ አልተናገርሁምም።
አምላካችን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይናገራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።
በማለዳ ምሕረትህን፥ በሌሊትም እውነትህን መናገር፥
መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም።
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ።
የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።