የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፥ መታመኛውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ብፁዕ ነው።
ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤ ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።
የቅድስናህን ግርማ ክብር ይናገራሉ፥ ተኣምራትህንም ይነጋገራሉ።
ሕዝቦች ስለ ክብርህና ስለ ግርማህ ታላቅነት ያወራሉ፤ እኔም ድንቅ ስለ ሆነው ሥራህ አሰላስላለሁ።
ይስሐቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያሰላሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይኖቹንም አቀና፤ እነሆም ግመሎች ሲመጡ አየ።
ለእግዚአብሔር ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ እግዚአብሔርም ያደረገውን ተአምራቱን ሁሉ ተናገሩ።
የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?
ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
ነገር ግን ስለ ሽንገላቸው አቈየሃቸው፥ በመነሣታቸውም ጣልኻቸው።
እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤ ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ።