እግዚአብሔር ይቅር ባይና መሓሪ ነው፥ መዐቱ የራቀ፥ ምሕረቱ የበዛ እውነተኛ ነው፤
አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።
እነርሱ ከቶ እውነት አይናገሩም፤ ቀኝ እጃቸውን አንሥተው የሚምሉት በሐሰት ነው።
አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፥ “ሰማይንና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አደርጋለሁ፤
እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።
ወደ ሰማይ ይወጣሉ፥ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፤ ሰውነታቸውም በመከራ ቀለጠች።
እስከ መቼ በነፍሴ ኀዘንን አኖራለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁልጊዜ ትጨነቅብኛለች? እስከ መቼ ጠላቶች በላዬ ይታበያሉ?
ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ አቤቱ በዮርዳኖስ ምድር፥ በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
እነሆ፥ ነፍሴን አድድነዋታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተነሡ፤ አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኀጢአቴም አይደለም።
እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆችን አነሣለሁ።
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ በቀኜ እምላለሁ፦ ለዘለዓለምም እኔ ሕያው ነኝ እላለሁ።