መዝሙር 144:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቸርነትህን ብዛት መታሰቢያ ይናገራሉ፥ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅህን ከላይ ዘርጋ፤ ከኀይለኛ ውሃ፣ ከባዕዳንም እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅህን ከላይ ስደድ፤ ከጥልቅ ውሃ ውስጥ ስበህ አውጣኝ፤ ታደገኝም፤ ከባዕዳን ኀይል አድነኝ። |
የእስራኤልም ልጆች ከባዕድ ሕዝብ ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፤ ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ተናዘዙ።
ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥ ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።