“ኀይልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግርማህንም ይነጋገራሉ፥ ብርታትህንም ያስረዳሉ።
የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥ ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።
የመብረቅ ብልጭታን ልከህ ጠላቶችህን በትናቸው፤ ፍላጻዎችህንም በመወርወር አሳዳቸው።
ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤
እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው፥ እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ይረዳታል።
ከተአምራትህ የተነሣ አሕዛብ ይደንግጣሉ፥ በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ፤ በጥዋት ይወጣሉ፥ ማታም ይደሰታሉ።
ለመከራ እሰበስባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎችንም እጨርስባቸዋለሁ።
ከተወጉት፥ ከተማረኩትም ደም፥ ፍላጻዎቼን በደም አሰክራለሁ፤ ከጠላት አለቆችም ራስ ሰይፌ ሥጋን ትበላለች።