እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ምስጋናውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታላቅነቱም ዳርቻ የለውም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?
አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው? ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ያኽል የምትንከባከበው ሰው ምንድን ነው? ይህን ያኽልስ የምታስብለት የሰው ልጅ ምንድን ነው?
ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ማን ነው?
ሰው ምንድን ነው? ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ፥ ልቡናውንም ትጐበኘው ዘንድ፥
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
ከመላእክት ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።
እስትንፋሱ በአፍንጫው ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
ነገር ግን መጽሐፍ እንዲህ ብሎ የመሰከረበት ስፍራ አለ፤ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?