መዝሙር 143:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆቼን ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤ ደረቅ ምድር ውሃ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ነፍሴ አንተን ተጠማች። |
ወይም ጌታውን እንደሚፈራ አገልጋይ ጥላውንም እንደሚመኝ፥ ወይም ደመወዙን እንደሚጠብቅ ምንደኛ አይደለምን?
ሙሴም፥ “ለፈርዖን ከከተማ በወጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐድጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረዶውም፥ ዝናቡም ደግሞ አይወርድም።
በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።