Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 143:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እጆቼን ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤ ደረቅ ምድር ውሃ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ነፍሴ አንተን ተጠማች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 መብ​ረ​ቆ​ች​ህን ብልጭ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ በት​ና​ቸ​ውም፤ ፍላ​ጾ​ች​ህን ላካ​ቸው፥ አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 143:6
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች።


“ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣


ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።


ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ።


የአምላካችንን ስም ረስተን፣ እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣


ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤ የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል። ቀበሮዎች በተኙባቸው ጕድጓዶች፣ ሣር፣ ሸንበቆና ደንገል ይበቅልበታል።


የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤


ሙሴም መልሶ፣ “ከከተማዋ በወጣሁ ጊዜ፣ እጆቼን ለጸሎት ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ መብረቁ ያቆማል፤ ከእንግዲህ በኋላ በረዶ አይኖርም።


የምሽትን ጥላ እንደሚመኝ አገልጋይ፣ ደመወዙንም እንደሚናፍቅ ምንደኛ፣


ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ።


ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን? የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios