Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሙሴም መልሶ፣ “ከከተማዋ በወጣሁ ጊዜ፣ እጆቼን ለጸሎት ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ መብረቁ ያቆማል፤ ከእንግዲህ በኋላ በረዶ አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሙሴም፥ “ከከተማ በወጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር እንደሆነች ታውቅ ዘንድ ነጎድጓዱ ይቀራል፤ በረዶውም ደግሞ አይወርድም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 9:29
19 Referencias Cruzadas  

“ምድር በመ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናትና።”


እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


መብ​ረ​ቆ​ች​ህን ብልጭ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ በት​ና​ቸ​ውም፤ ፍላ​ጾ​ች​ህን ላካ​ቸው፥ አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸ​ውም።


ማና​ቸ​ውም ሰው የል​ቡን ሕመም ዐውቆ ጸሎ​ትና ምህላ ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ቆሞ እጆ​ቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ።


እነሆ፥ ሰማይ፥ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም፥ ምድ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


እን​ግ​ዲህ “ይህ ለጣ​ዖት የተ​ሠዋ ነው” ያላ​ችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገ​ራ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም የሚ​ጠ​ራ​ጠር ስለ​ሆነ አት​ብሉ።


ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ደስ​ታ​ንና ማዳ​ን​ህን ስጠኝ፥ በጽኑ መን​ፈ​ስም አጽ​ናኝ።


አንተ ልብ​ህን ንጹሕ ብታ​ደ​ርግ፥ እጆ​ች​ህ​ንም ወደ እርሱ ብት​ዘ​ረጋ፥


በሠ​ር​ክም መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ልብ​ሴና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያዬ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ከመ​ዋ​ረዴ ተነ​ሣሁ፤ በጕ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ር​ክኬ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ዘረ​ጋሁ።


አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።


ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ከከ​ተማ ወጣ፤ እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረጋ፤ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም፥ በረ​ዶ​ውም ጸጥ አለ፤ ዝና​ቡም በም​ድር ላይ አላ​ካ​ፋም።


በዚ​ያም ቀን የም​ድር ሁሉ አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝቤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትን የጌ​ሤ​ምን ምድር እለ​ያ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስ​ድ​ስት ቀን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ ፈጥሮ በሰ​ባ​ተ​ኛዋ ቀን ዐር​ፎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ን​በ​ትን ቀን ባር​ኮ​ታል፤ ቀድ​ሶ​ታ​ልም።


አሮ​ንም በግ​ብፅ ውኆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ወጡ፤ የግ​ብ​ፅ​ንም ሀገር ሸፈኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios