አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
መዝሙር 139:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁልጊዜ በልባቸው ዐመፃን የሚመክሩ፥ ይገድሉኝ ዘንድ ይከብቡኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፥ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሣ ታውቃለህ፤ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ። |
አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእስራኤል ሀገር ነቢዩ ኤልሳዕ ያለ አይደለምን? በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውንና ቃልህን ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ እርሱ ይነግረዋል፤” አለ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህን ነገር ተናግራችኋል፤ እኔም የሰውነታችሁን በደል አውቃለሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር ለጎግ እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ፥ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎች በእስራኤል ነቢያት እጅ በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?
የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
ዛሬ ወደ ማልሁላቸው ምድር ገና ሳላገባቸው ክፋታቸውን አውቃለሁና፥ ከአፋቸውና ከልጆቻቸውም አፍ አትረሳምና ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት በደረሰባቸው ጊዜ ይህች መዝሙር ምስክር ሆና በፊታቸው ትቆማለች።”