አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ፤ ከትልልቆች ጋር፥ ከእኔም ይልቅ ከሚከብሩ ጋር አልሄድሁም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ።
የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከጥልቅ ሐዘን የተነሣ ወደ አንተ እጮኻለሁ።
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ።
በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቻችንን ወደ አንተ አነሣን።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
በእግዚአብሔር የታመኑ እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው፥ በኢየሩሳሌም የሚኖር ለዘለዓለም አይታወክም።
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ቤትን የሚሠሩ በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የሚጠብቁ በከንቱ ይተጋሉ።
እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው።
እስራኤል እንዲህ ይበል፥ “ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤
አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።