አሁንም ቅሬታ ይተዉልን ዘንድ፥ በተቀደሰውም ስፍራው ኀይልን ይሰጠን ዘንድ፥ አምላካችንም ዐይናችንን ያበራ ዘንድ፥ በባርነትም ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጥቂት ዕረፍትን አገኘን።
መዝሙር 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ተስተካክሎ በአንድነት ዐመፀ፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም፤ አንድም እንኳ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ ስማኝም። የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤ የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ ብርታቱን ስጠኝ። |
አሁንም ቅሬታ ይተዉልን ዘንድ፥ በተቀደሰውም ስፍራው ኀይልን ይሰጠን ዘንድ፥ አምላካችንም ዐይናችንን ያበራ ዘንድ፥ በባርነትም ሳለን ጥቂት የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ ለጥቂት ጊዜ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጥቂት ዕረፍትን አገኘን።
በሞቃቸው ጊዜ እንዲዝሉ፥ የዘለዓለምም እንቅልፍ እንዲተኙ መጠጥን አጠጣቸዋለሁ፤ አሰክራቸዋለሁም፤ ከዚያም በኋላ አይነቁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹሞችዋን፥ ኀያላኖችዋንም አሰክራለሁ፤ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ባማለ ጊዜ አልሰማም ነበር፤ እርሱም በእጁ ያለችውን በትር አንሥቶ ጫፍዋን ወደ ወለላው ነከረ፤ እጁንም ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።