አቤቱ፥ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?
ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
አራሾች በጀርባዬ ላይ አረሱ፥ ትልማቸውን አስረዘሙ።
ጀርባዬን በጅራፍ ተልትለው፥ የታረሰ ማሳ አስመስለውታል።
በቀንበር ትጠምደዋለህን? በእርሻህስ ውስጥ ትልም ያርስልሃልን?
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ ሰውነቴን ከእሥራት አውጣት፤ ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።
ጀርባዬን ለግርፋት፥ ጕንጬንም ለጽፍዐት ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከምራቅ ኀፍረት አልመለስሁም።
ወደ በደሉሽና ወደ አጐሰቈሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰውነትሽንም ዝቅ በዪ፥ ድልድይ አድርገን እንሻገርብሽ ወደሚሏት ሰዎች እጅ እመልሰዋለሁ።” በምድርም ላይ በሆድሽ አስተኙሽ፤ መንገደኞችም ሁሉ ረገጡሽ።