አቤቱ፥ ለቸሮች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣ ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥
ጐርፍ በወሰደን፥ ውሃም በሸፈነን ነበር፤
ብርሃኑም ጨለማ ሆነብህ፥ ተኝተህም ሳለህ ውኃው አሰጠመህ።
የቸርነትህን ብዛት መታሰቢያ ይናገራሉ፥ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።
ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም።
እነሆ፥ ኀያል ብርቱ የሆነ የእግዚአብሔር መቅሠፍት በኀይል እንደሚወርድ የበረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ወደ ምድር ይጥላል።
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ። መቅሠፍትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኀይለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመጣል።
ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤
አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።