የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
መዝሙር 123:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመዓት ቍጣቸውን በላያችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣ ማረን፤ እባክህ ማረን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፥ ብዙ ንቀት አጠግቦናልና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ብዙ ስድብ ስለ ደረሰብን ማረን! እባክህ ማረን! |
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
እነርሱም አሉት፥ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ እናትም ለማማጥ ኀይል የላትም።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አትሸከሚም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮችና ለኮረብቶችም፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆዎችም እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንአቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ።
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር፤ አለቆችም፥ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር።