Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ እና​ትም ለማ​ማጥ ኀይል የላ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነርሱም “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል ‘ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ለመውለድም ኀይል የለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 19:3
13 Referencias Cruzadas  

ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።


እኔ ተስ​ፋን ሰጠ​ሁሽ፤ አንቺ ግን አላ​ሰ​ብ​ሽ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሴት እን​ድ​ት​ወ​ልድ፥ መካ​ንም እን​ዳ​ት​ሆን የማ​ደ​ርግ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?” ይላል አም​ላ​ክሽ።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤ መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።


አቤቱ አንተ ይቅ​ር​ታ​ህን ከእኔ አታ​ርቅ፤ ቸር​ነ​ት​ህና እው​ነ​ትህ ዘወ​ትር ያግ​ኙኝ።


ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ፤


የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን የካ​ህ​ና​ቱ​ንም አለ​ቆች ማቅ ለብ​ሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።


ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እን​ደ​ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios