መዝሙር 121:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመፍረድ ዙፋኖቻቸውን በዚያ አስቀምጠዋልና፥ የዳዊት ቤት ዙፋኖች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጠባቂህ ነው፥ ጌታ በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ጠባቂህ ነው፤ በቀኝህም ሆኖ ያጠላልሃል። |
ለተዋረዱ ሰዎች ከተሞች ረዳት ሆነሃልና፥ በችግራቸው የተጨነቁትን በደስታ ጋረድሃቸው፤ ከክፉዎች ሰዎችም አዳንሃቸው፤ ለተጠሙት ጥላ ሆንሃቸው፤ ለተገፉትም ሕይወት ሆንሃቸው።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።