እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፥ አያንቀላፋምም።
በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣ በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።
እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።
በተሳለ የወታደር ፍላጻ ይወጋችኋል፤ በከሰል ፍምም ያቃጥላችኋል።
እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው፥ እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ይረዳታል።
እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።
ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮዋም እንደ ደነቈረ እባብ፥
ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
የሚገድል መርዝንም አዘጋጀበት፤ ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ።
ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል።
ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።
በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።
ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
አላዋቂ ሰው ለራሱ ክፋትን ይምሳል፥ በከንፈሩም እሳትን ይሰበስባል።
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ፤ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እንደዚሁ አደርጋለሁና።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”