ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
በእርሱ ዘንድስ ባለሟልነትን ያገኛልን? እግዚአብሔርንስ በጠራ ጊዜ ይመልስለታልን?
እንደ ሊባኖስ ላም ያከሳዋል። ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ልጅ ነው።
እግዚአብሔር በደሉን የማይቈጥርበት በልቡም ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ብያለሁና አጥንቶቼ አረጁ፤
ለድሃና ለምስኪን የሚያስብ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ከክፉ ቀን ያድነዋል።
አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ። ጽድቅህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።
“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌንም አዳመጥህ።
ዘወትር እንዲጸልዩ፥ እንዳይሰለቹም በምሳሌ ነገራቸው።
በምንም አትጨነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማልዱም፤ እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ።
በምስጋና እየተጋችሁ ለጸሎት ፅሙዳን ሁኑ።