መዝሙር 113:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደኋላው ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የጌታ ስም ይመስገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን! |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ። መቅሠፍትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ኀይለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመጣል።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።