La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 104:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ ተና​ገረ፥ የውሻ ዝንብ ትን​ኝም በም​ድ​ራ​ቸው ሁሉ መጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታ ክብር ለዘለዓለም ይሁን፥ ጌታ በሥራው ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔር ክብር ለዘለዓለም ይኑር! እግዚአብሔር በፈጠረው ነገር ሁሉ ደስ ይበለው።

Ver Capítulo



መዝሙር 104:31
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ነፍሱ ከእ​ርሱ ይወ​ጣ​ልና፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ኖ​ር​ምና ስፍ​ራ​ው​ንም ደግሞ አያ​ው​ቀ​ው​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በስ​ድ​ስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሥራ​ውን ፈጽሞ ስላ​ረፈ፥ በእ​ኔና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ነው።”


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።


ሁሉ ከእ​ርሱ፥ በእ​ር​ሱና ለእ​ርሱ ነውና፤ ለእ​ር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።


ለእ​ርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አሜን።


ለእ​ርሱ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በት​ው​ልድ ሁሉ ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


የሰ​ላም አም​ላክ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በእ​ና​ንተ እያ​ደ​ረገ ፈቃ​ዱን ታደ​ርጉ ዘንድ በመ​ል​ካም ሥራ ሁሉ ፍጹ​ማን ያድ​ር​ጋ​ችሁ፤ ለእ​ርሱ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ለእርሱ ክብርና ኀይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።