ከይሁዳም አለቆችና ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና እንዲህ አልኋቸው፥ “ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?
ምሳሌ 24:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ቃል ሰይፍ ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድን አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደለኛውን፣ “አንተ ጥፋተኛ ነህ” የሚሉት ግን መልካም ነገር ይገጥማቸዋል፤ የተትረፈረፈ በረከትም ይወርድላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚዘልፉት ግን ደስታ ይሆንላቸዋል፥ በላያቸውም መልካም በረከት ትመጣላቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደለኛውን በትክክል የሚቀጡ ዳኞች ግን መልካም ይሆንላቸዋል፤ ብዙ በረከትም ያገኛሉ። |
ከይሁዳም አለቆችና ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና እንዲህ አልኋቸው፥ “ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?
እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮዳሔ ልጆች አንዱ ለሐሮናዊው ለሰንባላጥ አማች ነበረ፤ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።
“ወንድምህን አትበድለው፤ በልብህም አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኀጢአት እንዳይሆንብህ ባልንጀራህን የምትነቅፍበትን ንገረው፤ ገሥጸውም።
ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።
ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ።