Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልጆቹ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ እን​ዳ​ደ​ረጉ ዐውቆ አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ው​ምና ስለ ልጆቹ ኀጢ​አት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤቱን እን​ደ​ም​በ​ቀል አስ​ታ​ው​ቄ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዔሊ በሚያውቀው ኀጢአት ምክንያት በቤተ ሰቡ ላይ ለዘላለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር፤ ልጆቹ አስጸያፊ ነገር አድርገዋል፤ እርሱ ግን አልከለከላቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልጆቹ በእኔ ላይ የንቀት ተግባር ሲፈጽሙ እርሱ ስላልገሠጻቸው ቤተሰቡን ለዘለዓለም እቀጣለሁ ብዬ ነግሬዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልጆቹ የእርግማን ነገር እንዳደረጉ አውቆ አልከለከላቸውምና ስለ ኃጢአቱ በቤቱ ለዘላለም እንድፈርድ አስታውቄዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 3:13
17 Referencias Cruzadas  

አባ​ቱም፥ “ከቶ ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” ብሎ አል​ከ​ለ​ከ​ለ​ውም ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ መልኩ እጅግ ያማረ ሰው ነበረ፤ እር​ሱ​ንም ከአ​ቤ​ሴ​ሎም በኋላ ወል​ዶት ነበር።


ንጉ​ሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ላይ የሠ​ራ​ኸ​ውን፥ ልብ​ህም ያሰ​በ​ውን ክፋት ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋ​ት​ህን በራ​ስህ ላይ ይመ​ል​ሳል።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ አት​ፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ው​ምን? ይህን የመ​ጣ​ብ​ንን ታላቅ ወገን መቃ​ወም እን​ችል ዘንድ ኀይል የለ​ንም፤ የም​ና​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ው​ንም አና​ው​ቅም፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ወደ አንተ ናቸው።”


ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥ ለመሳደብ ግን እጅህን አታንሣ፥


ብዙ ጊዜ ያበ​ሳ​ጭ​ሃ​ልና፤ በብዙ መን​ገ​ድም ልብ​ህን ያስ​ከ​ፋ​ታ​ልና፥ አንተ ደግሞ ሌሎ​ችን እንደ ረገ​ምህ ታው​ቃ​ለ​ህና።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ​ዚህ እንደ መን​ገዱ በየ​ሰዉ ሁሉ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢ​አ​ትም ዕን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ተመ​ለሱ።


አሁ​ንም ፍጻሜ በአ​ንቺ ላይ ደር​ሶ​አል። ቍጣ​ዬ​ንም እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


“አሕ​ዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ሸለ​ቆም ይውጡ፤ በዙ​ሪያ ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ እፈ​ርድ ዘንድ በዚያ እቀ​መ​ጣ​ለ​ሁና።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤


“ማንም ሰው ለአ​ባቱ ቃልና ለእ​ናቱ ቃል የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ ቢገ​ሥ​ጹ​ትም የማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ልጅ ቢኖ​ረው፥


የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን ይንቁ ነበ​ርና የዔሊ ልጆች ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበ​ረች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos