ምሳሌ 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣ ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመከራ ለማምለጥ የሚፈልግ፥ ክፉ ከመናገር ይቈጠባል። |
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።