በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
ምሳሌ 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ቂል ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንኛውም ሞኝ ተቈጥቶ ጠብ ማነሣሣት ይችላል፤ ሰውን የሚያስከብረው ግን ከክርክር መራቅ ነው። |
በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት፦ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።